Daydreams

country, upbeat, electro, electronic

June 9th, 2024suno

가사

[ምን ያደርጋ ገር … ? ሶረኔ - መስከረም - 2011) ምን ያደርጋል ሀገር፣ …. ምን ሊበጅ ዜግነት፣ ወልደው ካልሳሙበት፣ …. ዘርተው ካልቃሙበት፣ ህጻናት በመስኩ፣ …. አዛውንት በሸንጎ፣ …. ደምቀው ካልታዩበት፣ እምቦሳን በጓሮ፣ …. ጥገትቱን ከጨፌው፣ … ታስረው ካልዋሉበት፣ ጋማ ከብቱ በመስክ፣ … አውሬም በውርማ፣ … ሞልተው ካልታዩበት፣ ፏፏቴው በዳገት፣ … ጅረት በሸለቆ፣ … ሲፎክር ካልሰሙት፣ ተራራውም በደን፣ … ክምሩ ባውድማ፣ …. ገኖ ካልታየበት። ምንያደርጋል ሀገር ……? ከሰው ተወዳጅተው፣ … ከሰው ተዋውለው፣ …. ህይወት ካልመሩበት፣ ቅጠሉን በጥሰው፣ … አፈሩንም ልሰው፣ …. ቆመው ካልሄዱበት፣ አርሰው፣ አሳርሰው፣ …. ነግደው፣ አትርፈው … ሐብት ካልደረጀበት፣ ከእውቀትም ጨልፈው፣ … በሳይንስ ተራቀው፣ … ለድገት ካልሰሩበት፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ … መበለት፣ አዛውንት፣ … ካልተከበሩበት፣ ታመው ካልዳኑበት፣ … አርጅተው አፍጅተው፣ … ካልተቀበሩበት። ወጥተው ካልገቡበት፣ …. ሰርተው ካልኖሩበት፣ ከሸንጎው ዳኝነት፣ …. ከወንበሩ ፍትህ፣ …. ነጥፈው ከጠፉበት፣ መብት ሚዛን አጥቶ፣ …. ስርዓት ባገር ጠፍቶ፣ … እብሪት ከገዛበት፣ ዜግነት ከሀገር፣ …. ማንነት ከአንድነት፣ …. ሰላም ከመቻቻል፣ … ከተለያዩበት፣ ባሳብ ተደራጅተው፣ … ደግፈው ተቃውመው፣ … ውለው ካልገቡበት፣ በልዩነት ደምቀው፣ … በባህል፣ በእምነት፣ … ካልተከበሩበት። ምን ያደርጋል ሀገር ……? መውጣትና መግባት፣ …. መኖርና መስራት፣ … ከሚያስጨንቁበት፣ ያገር መውደድ ፍቅር፣ …. ነጻነት፣ አርነት፣ … ወንጀል ከሆነበት፣ ቃዬል በመንበሩ፣ … ይሁዳ ከልፍኙ፣ … ከሰለጠኑበት . ዜጋው ጠላት ሆኖ፣ … ዘራፊና ባእድ፣ …. ተከብረው ካሉበት፣ ስደትና ረሀብ፣ …. እስራትና ሞት፣ …. ዳረጎት ከሆኑት፣ በስልጣን መባለግ፣ …. በሀብት መንደላቀቅ፣ … ገነው ከታዩበት። የሰው ነፍስ ረክሶ፣ … በየጉራንጉሩ፣ …. ጭዳ ከሆነበት፣ ውንብድና ባገር፣ … ሸንጎ ተቀምጦ፣ … ህግ ካረቀቀበት፣ ከሐዲ በዙፋን፣ … ገንጣይ ባማካሪ፣ … ነግሰው ከኖሩበት፣ ጦቢያ ማለት ቀርቶ፣ …. ቋንቋ፣ የዘር ሐረግ፣ … ሀገር ከመሩበት . የእብሪት ማራገፊያ፣ … ያአምባገነን ቅርሻት፣ … መትፊያ ከሆኑበት . AD Download to read ad-free. 00:00 03:25 ምንስ ሀገር አለን ……! በስሟ እምንጠራት፣ …. ምን ወዳጅ ተጘኝቶ፣ … ወገኔ የሚሉት። ሲታመም ካላዩት፣ … ሲወድቅ ካላነሱት፣ … ሲሞት ካልቀበሩት፣ ሲቸገር ካልረዱት፣ …. ሲራብ ካልጎበኙት፣ …. ሲዳር ካላኮሩት፣ ሲበደል ሲጨቆን፣ ድምጽ ካልሆኑለት፣ እጅ ካልዘረጉለት በሸንጎ ተሟግተው፣ … መብቱን አስመልሰው፣ .. ካላስከበሩለት፣ ዘምተው ግዳይ ጥለው፣ … ወድቀው ተሰውተው፣ … ታሪክ ካልሰሩለት፣ ውርደቱን በክብር፣ ….. ጥቃቱንም በድል፣ … ታግለው ካልቀየሩት፣ ቢፎከር፣ ቢቅራሩ፣ … ሀገር ! ሀገር ! ቢሉት፣ … ዲስኩር ቢያበዙለት፣ ህንፃው ቢደረደር፣ … አስፋልቱ ቢነጠፍ፣ … ግድብ ቢሰሩለት፣ ምን ያደርጋል ታዲያ፣ … ምን ያደርጋል ሃገር፣ …. ያለሰው ቢወዱት። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

추천

Caminho de Luz
Caminho de Luz

rap, hip hop, dark

El Sueño de David
El Sueño de David

drill aggressive intense

Unbreakable Resolve
Unbreakable Resolve

Electronic Rock Industrial Metal Synthwave Robotic Female Vocals

Unraveled Ties
Unraveled Ties

male vocalist,rock,hard rock,progressive rock,melodic,energetic,ballad,passionate,classic rock,epic

Sunset at Cat Ba
Sunset at Cat Ba

melodic chill acoustic

Moonlit Stroll
Moonlit Stroll

lofi hip hop piano jazz

Golden DJ Days
Golden DJ Days

hip hop,west coast hip hop,hardcore hip hop,gangsta rap,g-funk

Chasin' Love
Chasin' Love

Country-EDM, progressive house, male voice

Sweat More, Bleed Less (Hybrid Remix)
Sweat More, Bleed Less (Hybrid Remix)

deep brass & percussion, hybrid orchestra technique, combines orchestral instruments with synthesizers & electric guitar

Neon Love
Neon Love

bossa nova bittersweet nostalgic citypop

Kuuh in the Rainbow Nation
Kuuh in the Rainbow Nation

Lo-Fi, electro swing, sax, upbeat, modern, clear voice

Милые арбалеты
Милые арбалеты

lo-fi bubblegum bass

Dance Till Dawn
Dance Till Dawn

synthwave anthemic

Birlikte Her An
Birlikte Her An

pop, beat, rap, reggae, children,

Escolhas e Consequências
Escolhas e Consequências

slap guitar flamenco r&b sentimental trap

יוני אחלה גבר
יוני אחלה גבר

אקוסטי עכשווי pop