
እናቴ
emotional gospel
May 4th, 2024suno
가사
የዘፍጥረቴ ብራና
እኔን የከተበባት፣
ህያው የፍቅር ማማ
እውነትም እናቴ... "እ".... ናት
በሕይወት አሳዶ ቁር
የሰው ልጅ ፍቅርን ቢያጣ፣
ከፍቅር የተወለደ
ሰው ማለት የፍቅር እጣ...
እያለ የሚያስተርከኝ
እውነትን የምዘምራት፣
የነፍሴ የፍቅር መክሊት፣
እውነትም እናቴ ... እ ..... ናት
...እ ..... ነሽ እናቴ ለኔ
የምጥሽ ሽራፊ ስቃይ!
በሐዘንሽ ጨለማ ነው
ፈገግታዬ ደምቆ “ሚታይ...
የአፈር ማቅረቢያው ማዕድ
የፈጣሪ ትፍታ አልፋ፣
ይሄ ያማረ ስጋ ባንችው ነው
ደልቶት የፋፋ...
ፍቅርሽን ተናገር ብባል
ልመስልሽ ብጥር ከዓለም፣
ባጭሩ ከ"እ"ታ በቀር
ውስጤ ውስጥ ሌላ ቃል የለም !
የዘፍጥረቴ ብራናና
እኔን የከተበባት፣
ህያው የፍቅር ማማ
እውነትም እናቴ... "እ እ እ እ እ".... ናት
በሕይወት አሳዶ ቁር
የሰው ልጅ ፍቅርን ቢያጣ፣
ከፍቅር የተወለደ
ሰው ማለት የፍቅር እጣጣ...
እያለ የሚያስተርከኝ
እውነትን የምዘምራት፣
የነፍሴ የፍቅር መክሊት
እውነትም እናቴ ... እ እ እ..... ናት
...እ ..... ነሽ እናቴ ለኔ
የምጥሽ ሽራፊ ስቃይ!
በሐዘንሽ ጨለማ ነው
ፈገግታዬ ደምቆ “ሚታይ...
የአፈር ማቅረቢያው ማዕድ
የፈጣሪ ትፍታ አልፋ፣
ይሄ ያማረ ስጋ
ባንችው ነው ደልቶት የፋፋ...
ፍቅርሽን ተናገር ብባል
ልመስልሽ ብጥር ከዓለም፣
ባጭሩ ከ..."እ"...ታ በቀር
ውስጤ ውስጥ ሌላ ቃል የለም !
እንደው ግን በምድር ቋንቋ
በማየው ምስል ስመስልሽ፣
እማማ ካንችው በስተቀር
አንችን መሰል የለም ስልሽ፣
እማምዬ ልሙትልሽ!!!....
እንደ ጣና ተንጣሎ
እንደ ሶፍ ዑመር በልቤ
ጥልቅ ፍቅሩን የተከለ፣
እማማ ካንችው ቃል ሌላ
በምድር ምን ታምር አለ ?!!
እንደ ትዝታ አንች ሆዬ
ረቂቅ ዜማ ነው ፍቅርሽ፣
ምንም አይኑርሽ ግዴለም
ይበቃል እናትነትሽ፣
እማምዬ ልሙትልሽ ....!!!
ቃሌን አይደለሽም እማ...
እንዲህ እና እንዲያ ስላልኩሽ፣
እንዲህም እንዲያም ባትሆኝ..
ይበቃል እናትነትሽ !
እማምዬ ልሙትልሽ!!!....
እማምዬ ልሙትልሽ!!!....
እንደ ጣና ተንጣሎ
እንደ ሶፍ ዑመር በልቤ
ጥልቅ ፍቅሩን የተከለ፣
እማማ ካንችው ቃል ሌላ
በምድር ምን ታምር አለ ?!!
..............
........
......
እንደ ትዝታ አንች ሆዬ
ረቂቅ ዜማ ነው ፍቅርሽ፣
ምንም አይኑርሽ ግዴለም
ይበቃል እናትነትሽ፣
እማምዬ ልሙትልሽ ....!!!
እማምዬ ልሙትልሽ ....!!!
ቃሌን አይደለሽም እማ...
እንዲህ እና እንዲያ ስላልኩሽ፣
እንዲህም እንዲያም ባትሆኝ..
ይበቃል እናትነትሽ !
እማምዬ ልሙትልሽ ....!!!
እማምዬ ልሙትልሽ ....!!!
추천

It's Chilly In This Grave
bossa nova smooth relaxing

City Lights
experimental trippy Khyal voices with hamon and minimoog electronic modular organ

najlepszy dzien ?
Boom bap, pop, big room

Desert Fire
middle eastern beats arabic rap

Tomorrow’s Another Day
anime acoustic lofi

I'm a wild fire
an edgy uk reggae rap song,bass drop,crescendo,melodic

Новая Эра
акустическая киберпанк

Disco Dream
disco rhythmic soulful

Lost Pup
electronic japanese underground rap gritty

Bum bum
Pop dance techno piano violins powerful female voice

Monsters in the Deep
electronic ambient chill

BattleCry5
epic hard rock heavy

Rainy Cafe
a chilling rainy cafe mood lofi

Yorkie Boys
Rhythmic doo wop, fast, bouncy, swing, barbershop quartet

Thank You
dreamy pop (male voice)

Eternal Echoes
emotional orchestral electronic

